Fana: At a Speed of Life!

የቶኪዮ ኦሊምፒክ በነገው እለት ይጀምራል

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በስፖርት አፍቃሪው ዘንድ በጉጉት የሚጠበቀው የ2020 የቶኪዮ ኦሊምፒክ በነገው እለት ይከፈታል፡፡

በዘንድሮው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ከ205 ሀገራት የተውጣጡ ከ11 ሺህ በላይ የኦሊምፒክ አትሌቶች በ33 አይነት ስፖርቶች ይሳተፋሉ፡፡

በውድድሩ ለአሸናፊዎች 5 ሺህ የተለያዩ ሜዳሊያዎች የተዘጋጁ ሲሆን፥ ሜዳሊያዎቹ ጥቅም ላይ ከዋሉ መገልገያ ቁሳቁሶች የተዘጋጁ መሆናቸውን የቢቢሲ እና ፍራንስ 24 ዘገባ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያ በኦሊምፒኩ በአትሌቲክስ፣ በውሃ ዋና፣ በብስክሌት እና ቴኳንዶ ትሳተፋለች፡፡

በተለይም በአትሌቲክሱ ዘርፍ ኢትዮጵያ የሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ እንደምትገባም ይጠበቃል፡፡

ኢሊምፒኩ ከዓለም አቀፉ የጤና ስጋት ከሆነው ኮቪድ19 ጋር በተያያዘ ያለተመልካች እንደሚካሄድ አዘጋጅ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡

ከዚህ ጋር ተያይዞም ከየሃገራቱ የመጡ ተወዳዳሪ አትሌቶች በየቀኑ የኮቪድ19 ምርመራ የሚደረግላቸው ይሆናል፡፡

ለኦሊምፒክ ዝግጅቱ ከ14 ነጥብ 8 ቢሊየን ዶላር በላይ ወጪ መደረጉንም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ከይፋዊው የመክፈቻ መርሃ ግብር ቀደም ብሎ የእግር ኳስ ጨዋታዎች የተካሄዱ ሲሆን፥ በወንዶች በተደረገ ጨዋታ ጀርመን በብራዚል፣ አርጀንቲና በአውስትራሊያ እንዲሁም ፈረንሳይ በሜክሲኮ ተሸንፈዋል፡፡

በሌላ በኩል ግብጽ ከስፔን ያለምንም ጎል አቻ ሲለያዩ፥ ኒውዚላንድ ደቡብ ኮሪያን፣ አይቮሪኮስት ሳዑዲ አረቢያን፣ ጃፓን ደቡብ አፍሪካን እንዲሁም ሮማኒያ ሆንዱራስን በማሸነፍ ውድድሩን በድል ጀምረውታል፡፡

ሌሎች የኦሊምፒክ ውድድሮችም እስከ ፈረንጆቹ ሃምሌ 8 የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.