Fana: At a Speed of Life!

207 የወተት አይነቶችን በማዘጋጀት ክብረ ወሰን የሰበረው ምግብ ቤት

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) 207 የወተት አይነቶችን በማዘጋጀት ለደንበኞቹ ያቀረበው ምግብ ቤት ስሙን በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ (ጊነስ ቡክ ኦፍ ሪከርስ) ውስጥ ማስፈር ችሏል።

በደቡብ አፍሪካ ኬፕታወን ከተማ የሚገኘው ጊብሰን ምግብ ቤት ተገቢውን መስፈርት ያሟሉ እና የተለያየ ጣዕም ያላቸው 207 የወተት አይነቶችን ለገበያ ማቅረቡ ብዙዎችን አስገርሟል።

ምግብ ቤቱ ስሙን በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ውስጥ ለማስፈር ከአንድ ዓመት ተኩል በላይ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን አስታውቋል።

ባሳለፍነው ጥቅምት ወር ላይ የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ዳኞች በተገኙበት እያንዳንዱን የወተት አይነት የሚያሳይ ፕሮግራም ማካሄዱን አስታውሷል።

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ድርጅት ዳኞችም የቀረቡት የወተት አይነቶች ጣዕም እና ይዘት ተገቢውን መስፈርት ያሟላ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በዚህም ምግብ ቤቱ በርካታ አይነት የወተት አይነቶችን ለደንበኞቹ በማቅረብ ክብረ ወሰን ለመስበር ያደረገው ሙከራ መሳካቱን የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ድርጅት ይፋ አድርጓል።

ምንጭ፦ www.upi.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.