Fana: At a Speed of Life!

ረጅሙ የቦይንግ 777-9 ኤክስ አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን በስኬት አጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ረጅሙ የቦይንግ አውሮፕላን የመጀመሪያ በረራውን በስኬት አጠናቋል።

ቦይንግ 777- 9 ኤክስ የተሰኘው ይህ አውሮፕላን ባለ ሁለት ሞተር እና 76 ሜትር ርዝመት እንዳለው ተገልጿል።

አዲሱ አውሮፕላን በኩባንያው ምርቶች ላይ በሚፈጠሩ እክሎች ምክንያት የሚደርሱ አደጋዎችን ለመቀነስ ያስችላል ነው የተባለው።

የአውሮፕላኑ የተሳካ የበረራ ሙከራ ሲያትል ከተማ አካባቢ የተከናወነ ሲሆን፥ ይህ ሙከራ ከመካሄዱ በፊት በአየር ፀባይ ችግር ምክንያት ሊካሄዱ የነበሩ ሁለት የሙከራ በረራዎች እንዲቋረጡ ተደርጓል።

ኩባንያው እስካሁን 309 የሚሆኑ 777 ኤክስ አውሮፕላኖችን የሸጠ ሲሆን፥ የአንዱ ዋጋም 442 ሚሊየን ዶላር ነው ተብሏል።

ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላኖቹ ላይ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ንብረትነታቸው የኢትዮጵያ እና ኢንዶኔዢያ የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች ተከስክሰው የ346 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎም ኩባንያው የሚያመርታቸው አውሮፕላኖች ደህንነት አስተማማኝ አይደለም በሚል በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና በባለሙያዎች ከፍተኛ ወቀሳ ሲቀርብበት ቆይቷል።

ምንጭ፦ ሲ ኤን ኤን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.