Fana: At a Speed of Life!

የጸጥታው ምክር ቤት የህዳሴው ግድብ ድርድር በአፍሪካ ህብረት እንዲታይ ድጋፉን ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጸጥታው ምክር ቤት የህዳሴው ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር በአፍሪካ ህብረት እንዲታይ ወሰነ።

ምክር ቤቱ ትላንት ማምሻውን በካሄደው ስብሰባ ÷ የግድቡ ድርድር አሁን እየተካሄደ ባለው በአፍሪካ ህብረት በኩል እንዲካሄድ ያለውን ድጋፍ ገልጿል፡፡
ግብፅ የተለያዩ ምክንያቶች ለመከራከሪያ ነት አቅርባለች።
የኢትዮጵያ መከራከሪያ ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እና በጋራ መልማትን ነው መርህ ያደረገችው።
የታችኞቹ የተፋሰስ ሀገራት ላይ የጎላ ጉዳት የማያደርስ እንደሆን ደጋግማ ብትገልጽም ግብጽና ሱዳን ጉዳዩን አለማቀፋዊና የጸጥታ ጉዳይ አደርገውታል።
በጸጥታው ምክር ቤት ጉዳዩ እንዲታይ የቀረበውን ክርክር ያደመጠው የጸጥታው ምክር ቤት ደርድሩ በአፍሪካ ህብረት እንዲታይ ድጋፉን ገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.