Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ከ3 በላይ የውጭ ሀገር ተጫዋቾችን ማስፈረም እንደማይቻል ፌዴሬሽኑ አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ  እግር ኳስ ፌዴሬሽን የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ዝውውርን የተመለከተ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዚህም ፌዴሬሽኑ በ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን በየትኛውም የፕሪሚየር ሊግ ክለብ ከ3 በላይ የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ማስፈረም እንደማይቻል ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ቀደም ሲል በነበረው የውጭ ሀገር ተጫዋቾች የዝውውር መመሪያ መሠረት አንድ ክለብ እስከ አምስት ድረስ የውጭ ሀገራት ተጫዋቾች የሚያስፈርምበት አሰራር ከ2014 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ ቁጥሩን በመቀነስ 3 ተጫዋቾች ብቻ ማስፈረም የሚችሉ መሆናቸውን ፌዴሬሽኑ በዛሬው እለት አሳውቋል፡፡

በተጨማሪም በከፍተኛ እና በ1ኛ (በብሔራዊ ሊግ) ተሳታፊ የሚሆኑ ክለቦች  ምንም ዓይነት የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ማስፈረም የማይቻሉ መሆኑን ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.