Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ከሚገኙ የግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በክልሉ ከሚገኙ የግብረሰናይ ድርጅቶች ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው የመንግስትና የግብረሰናይ ድርጅቶች ግንኙነት መጠናከር፣ የአፋጣኝ ምላሽ መስጠት እቅድና ዝግጅት፣ በክልሉ ባሉ ጫናዎችና ችግሮች ዙሪያ መክረዋል።
በክልሉ በድርቅ ፣ በጎርፍ አደጋና ግጭት ከቀያቸው በተፈናቀሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ዙሪያም በውይይት መድረኩ የተለያዩ ሀሳቦች ተነስተዋል፡፡
በዓለም አቀፍ ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከሰተው ኮቪድ19ና የዋጋ ንረት አማካኝነት በክልሉ የሚገኙ አቅማቸው አነስተኛ የሆኑ ዜጎችን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ፈተና መሆኑም በመድረኩ ተንፀባርቋል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በክልሉ ዘንድሮ የዝናብ እጥረት ሊኖር ስለሚችል የግብረሰናይ ድርጅቶች ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት ድርቅ ከመከሰቱ ቀደም ብሎ ዝግጅቶች እንዲጠናከሩ ማድረግ እንዳለባቸው አቶ ሙስጠፌ መናገራቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.