Fana: At a Speed of Life!

ኮርፖሬሽኑ ከሁለት የንግድ ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት ተስማማ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከአዋሽ ባንክና ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር በጋራ መስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው እንዲሁም የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጸሀይ ሽፈራው ፈርመዋል፡፡
ለኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች የብድር አቅርቦት ማረጋገጥ አንዱ የስምምነቶቹ አካል ሲሆን ኮርፖሬሽኑ ለሚያከናውናቸው የቢዝነስ ስራዎች የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ የፕሮጀክት ብድሮችን ለማቅረብም ስምምነት ደርሰዋል፡፡
ስምምነቶቹ የኮርፖሬሽኑን የገንዘብ አቅም በማሳደግ እና ፕሮጀክቶችን በፍጥነት ለማስፈፀም ተጨማሪ አቅም ከመፍጠር ባሻገር በተቋማቱ መካከል ስትራቴጂካዊ አጋርነት በመፍጠር ኮርፖሬሽኑ ለሰራተኞቹ ምቹ የኑሮ ሁኔታን በመፍጠር የስራ መነቃቃት እና ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጾ እንደሚኖረው መጠቆሙን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.