ባለፉት 11 ወራት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ከመሬት ይዞታና ምዝገባ ተገኘ
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ ባለፉት 11 ወራት 1 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ከመሬት ይዞታና ምዝገባ አግኘቻለሁ አለ፡፡
በ 11 ወራት ውስጥ ብቻ የተገኘው ገቢ ከ2012 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ4 እጥፍ እንደሚበልጥ የተናገሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ዘሪሁን አምደማሪያም ናቸው፡፡
በአስሩም ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በዘረጋው አገልግሎት ከ111 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችና የመሬት ይዞታዎችን አረጋግጦ በመመዝገብ ያገኘው ገቢ እንደሆነ ኤጀንሲው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ከላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የተቋሙን የቴክኖሎጅ አጠቃቀም ስርዓት በማዘመን፣ ቀልጣፋና ውጤታማ የአገልግሎት አሰጣጥን ሂደት በሶስት እጥፍ በማሳደግ የተገልጋዮችን እንግልትና ምልልስ መቅረፋቸው ለገቢው ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳበረከተም ተናግረዋል፡፡
የተጀመሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ስራዎች ወቅቱን ያገናዘበ የቴክኖሎጅ በመጠቀም የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!