Fana: At a Speed of Life!

ብልጽግና ፓርቲ እና የቬትናም ገዢ ፓርቲ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ብልጽግና ፓርቲ እና የቬትናም ገዢ ፓርቲ በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽህፈት ቤት ውይይት አድርገዋል፡፡

በብልጽግና ፓርቲ የህዝብና ውጭ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ቢቂላ ሁሪሳ፥ በኢትዮጵያ አዲስ ከተሾሙት የቬትናም አምባሳደር ንጉዬን ናም ታይን ጋር በጋራ ጉዳዮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸዋል፡፡

ዶክተር ቢቂላ አያይዘውም፥ ብልጽግና ፓርቲ ከቬትናም ገዢ ፓርቲ ጋር በመረጃ ልውውጥ፣ በስልጠና እና በሌሎች የአቅም ግንባታ ስራዎች ዙሪያ በጋራ በመስራት ለሁለቱ አገራት የጋራ ብልጽግና መተባበር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የቬትናም ገዢ ፓርቲ እና የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በቬትናም ተገኝተው በሁለቱ ፓርቲዎች ትብብር ዙሪያ እንዲመክሩ ግብዣ መደረጉን ከብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.