Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህዝበ ውሳኔ ተዓማኒና ነፃ እንዲሆን የሕዝበ ውሳኔ አስተባባሪዎች ሃላፊነት መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ  ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ህዝበ ውሳኔ ነጻ ፣ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ ፣ሠላማዊ በህዝቡ ዘንድ ተዓማኒነትን ያተረፈ እንዲሆን የህዝበ ውሳኔው አስተባባሪ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሃላፊነት መሆኑ ተገልጿል።

ለደቡብ  ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የሕዝበ ውሳኔ አስተባባሪ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በዚህ ወቅት የተገኙት የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ ከለውጡ ስኬቶች መካከል በደቡብ ክልል የሚገኙ  የዳውሮ፣የከፋ፣የቤንች ሽኮ፣የሽካ፣የምዕራብ ኦሞ ዞኖችና የኮንታ ልዩ ወረዳ ህዝቦች አንድ ላይ ክልል ለመመስረት እንዲፈቀድላቸው ያቀረቡት ጥያቄ በፌዴሬሽን ምክር ቤት ተቀባይነት ማግኘቱና ይህም በሕዝበ ውሳኔ እንዲረጋገጥ መወሰኑ ነው ማለታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለህዝበ ውሳኔው ስራ መሳካት በደቡብ ክልል መንግሥት እውቅና በተደራጀው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የውሳኔ ሕዝብ አስተባባሪ የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ባለሙያዎች በሕገመንግሥትና በፌደራል ስርዓት ላይ ስልጠናው  መሠጠቱ የሚደረገው ሕዝበ ውሳኔው  ነጻ ፣ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊ ፣ሠላማዊ በሕዝቡ ዘንድ ተዓማኒነትን ያተረፈ እንዲሆን እንደሚያስችልና የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሃላፊነቱን መወጣት እንዳለበት ገልፀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.