6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሊራዘም ይችላል- ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ከተያዘለት ጊዜ ከ2 እስከ 3 ሣምንታት ሊራዘም እንደሚችል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል፡፡
ቦርዱ በመራጮች ምዝገባ ሂደት እና ባጋጠሙ ችግሮች ዙሪያ ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር እየተወያየ ነው።
የቦርዱ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱኳን ሚደቅሳ ምርጫ ጣብያዎችን በመክፈት በመራጮች ምዝገና በሌሎች ስራዎች ላይ የተፈጠረው መዘግየት የድምጽ መስጫ ቀኑን ሊገፋው ይችላል ሲሉ ጠቁመዋል፡፡
በሌላ በኩል የፌደራል የድምጽ መስጫ ቀን ከአንድ ሳምንት በኋላ ሊደረግ የነበረው የአዲስ አበባና የድሬዳዋ ድምጽ መስጫ ቀን በአንድ ቀን እንዲሆን ተወስኗል፡፡
በመድረኩም እስካለፈው ረቡዕ ግንቦት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በተደረገ የመራጮች ምዝገባ ከ36 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
በትግስት አብረሃም
ተጨማሪ መረጃ ከኢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!