Fana: At a Speed of Life!

የትምህርት ሚኒስቴር ራሳ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር በህንድ ነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስቴር ራሳ ከተሰኘ የግል ኩባንያ ጋር በህንድ ነፃ የትምህርት እድል ለመስጠት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርሟል።

የነፃ የትምህርት እድሉ ከአጫጭር ስልጠና እስከ ፒ ኤች ዲ የሚደርሱ ፕሮግራሞችን የያዘ ነው ተብሏል።

ስምምነቱን የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ገረመው ሁሉቃ እና የራሳ ማኔጅመንት እና የማማከር ድርጅት ስራ አስኪያጅ ዶክተር ራጃሽ ሞሲስ ተፈራርመዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው የትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንን አቅም ለማሳደግ በሚያደገው ጥረት ውስጥ እንዲህ ያሉ የነፃ የትምህርት እድሎች ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ኩባንያው ከዚህ በፊት ከ1 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች በህንድ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የትምህርት ደረጃዎች እና መስኮች ነፃ የትምህርት እድል ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

በቀጣይ ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል እንደሚሰጥ የራሳ ማኔጅመንት ስራ አስኪያጅ ዶክተር ራጃ ሞሲስ መጥቀሳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

ነፃ የትምህርት እድሎቹ ህንድ በሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ ሲሆን፣ አጫጭር ስልጠና፣ የዲግሪ፣ የማስተርስ እና የፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞችን ያካተቱ ናቸው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.