ቻይና ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት ድጋፍ አደረገች
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 6፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይና ጦር ሃይል ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት መድሀኒትና የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።
በድጋፍ ርክክቡ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታን ጨምሮ የመከላከያ ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ማርታ ሉዊጂ እንዲሁም ከፍተኛ የጦር መኮንኖች ተገኝተዋል፡፡
የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ የቻይና መንግስት ከሀገር መከላከያ ጋር በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀው በቅርቡ የተባበሩት መንግስታት በኢትዮጵያ ዙሪያ ባደረገው ስብሰባ ቻይና ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም ላሳየችው ቁርጠኝነት አመስግነዋል።
በኢትዮጵያ የቻይና አምሳደር ዣዎ ዢያን በበኩላቸው የቻይና የጦር ሀይል ለኢትዮጵያ መከላከያ ያደረገው ድጋፍ በሁለቱ ወዳጅ ሀገራት መካከል ያለውን የቆየ ወዳጅነት ማሳያ ነው ብለዋል።
አምባሳደሩ የቻይናና ኢትዮጵያ ወታደራዊ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ይህም በሁለቱ ሀገራት አመራሮች የተፈረመው የስትራቴጂክ ግንኙነት አንዱ አካል መሆኑን መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!