አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዚዳንት ራማፎሳ ጋር ያደረጉት ውይይት ስኬታማ ነበር – አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም
አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ ጋር ያደረጉት ውይይት ውጤታማ እንደነበር በደቡብ አፍሪካ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዶክተር ሽፈራው ተክለማርያም ተናገሩ፡፡
አምባሳደሩ ከፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ በውይይቱ ላይ ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ እንደሚያሻ መግባባት ላይ መድረሳቸውን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
በሁለትዮሽ ቀጠናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከመወያየት ባሻገር በቀጣይ አፍሪካ እንደአህጉር እየገባችበት ለሚገኙ ዓለም አቀፍ የግንኙነት መድረኮች አፍሪካውያን በትብብርና በጋራ በመቆም የአህጉሪቷን ጥቅም ሊያስከብሩ እንደሚገባ በውይይታቸው ተስማምተዋል፡፡
የአቶ ደመቀ ጉብኝት በቀጣይ ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር በሚያደርጉት ዘርፈ ብዙ ግንኙነቶች ላይ አመርቂ ውጤት ማስመዝገቡን አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡
በስላባት ማናዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!