Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት መግለጫ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን የሚጻረር አካሄድን አልቀበልም በማለቷ የመጣ ነው – አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ህብረት በ6ኛው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ታዛቢዎችን አልክም ማለቱ ኢትዮጵያ ሉዓላዊነትን የሚጻረር አካሄድን አልቀበልም በማለቷ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናገሩ፡፡

አምባሳደር ዲና ሳምንታዊ መግለጫ በዛሬው እለት ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም ህብረቱ ከኢትዮጵያ ኮሙዩኒኬሽን መሳሪያ ውጪ የራሴን ይዤ ልግባ ማለቱን አንስተው ለመግለጫው አንዱ ምክንያት ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከምርጫው ጋር በተገናኘ የምርጫ ቦርድን ተግባር እና ኃላፊነት የሚጸረር ጥያቄ አቅርቦ ውድቅ እንደተደረገበትም አስረድተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም ህብረቱ ለስድስተኛው ሀጋረዊ ምርጫ ታዛቢዎችን አልክም ማለቱን አውስተዋል፡፡

በምስክር ስናፍቅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.