በድሬዳዋ ዛሬ በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በድሬዳዋ ከተማ ሸመንተሪያ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ዛሬ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እስከ ስድስት ሰዓት በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የዘጠኝ ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
የሰዎቹ ህልፈት የተሰማው የአንድ ድርጅት አጥር ግንብ ፈርሶ በሶስት መኖሪያ ቤቶች ላይ በመውደቁ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡
ህይወታቸው ካለፉት መካከል የሶስት ወር ጨቅላ ህፃንን ጨምሮ ሶስቱ ህፃናቶች እንደሚገኙበት ምክትል ኢንስፔክትር ባንታለም ግርማ ገልጸዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን በአደጋው በደረሰው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል፡፡
አክሎም በድሬዳዋ ከወትሮው በተለየ መልኩ ዝናብ በከፍተኛ ሁኔታ እየጣለ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም የጎርፍ አደጋ ሊያስከትል የሚችል ስለመሆኑ ብሄራዊ ሜትሮሎጂ የገለፀ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ መላው ህብረተሰብ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ኮሚሽኑ ማሳሰቡን ከድሬ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!