የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቴፒ ቅርንጫፍ ከፈተ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በደቡብ ብሔር፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሸካ ዞን ቴፒ ያስገነባውን ቅርንጫፍ ከፈተ።
ቅርንጫፉ አቶ አንተነህ ፍቃዱ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ፥ የደቡብ ብሔር፥ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የግብርና ቢሮ ኃላፊና አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ፤ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ ተመርቆ ተከፍቷል።
በቅርንጫፉ በሸካ ዞን ለሚገኙ አራት ወረዳዎችና በጋምቤላ ብሔራዊ ክልል ማጃንግ ዞን ለሚገኙ ሁለት ወረዳዎች አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።
በህዝብ ጥያቄ መሰረት የዚህ ቅርንጫፍ መከፈት በሁለቱ ዞኖች የሚገኙ አርሶ አደሮችና አቅራቢዎች ምርታቸውን ወደ አቅራቢያ ቅርንጫፍ ለመውሰድ የሚያደርጉትን ተጨማሪ ጉዞ በአማካይ በ130 ኪሎ ሜትር ይቀንሳል፡፡
ሸካና ማጃንግ ዞኖች ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና የሚመረትባቸው አካባቢዎች በመሆናቸው የቅርንጫፉ መከፈት ጥራት ያለው ምርት ተመርቶ ለዓለም ገበያ እንዲቀርብ አስተዋጽኦ ያደርጋል መባሉን ከምርት ገበያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በትናትናው ዕለትም በሚዛን አማን ከተማ 24ኛ ቅርንጫፉን ከፍቷል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!