የሶማሊያው ፕሬዚዳንት የተራዘመ የስልጣን ዘመናቸውን በመሰረዝ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ /ፎርማጆ/ ለሁለት ዓመታት የተራዘመ የስልጣን ዘመናቸውን በመሰረዝ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንዲካሄድ ጥሪ አቀረቡ፡፡
ሰሞኑን ከተራዘመው የፕሬዚዳንቱ የስልጣን ዘመን ጋር ተያይዞ የእርሳቸው ደጋፊና ታቃወሚዎች ጎራ ለይተው ግጭት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል፡፡
ግጭቱን ተከትሎም ነዋሪዎች ቀያቸውን በመልቀቅ እየሸሹ እንደነበር ተገልጿል፡፡
ፕሬዚዳንቱ ዛሬ ለሃገሪቱ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር በሀገሪቱ ምርጫ እንዲካሄድ የወሰኑ ሲሆን የስልጣን ዘመኑን መራዘም የተቃወሙትን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሁሴንን አድንቀዋል፡፡
በርካቶች አልሻባብ በሀገሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም ችግር ይፈጥራል በሚል ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡
ምንጭ፦ ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!