በሀላባ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ ክልል ሀላባ ዞን ዌይራ ወረዳ ዛሬ ማለዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሁለት የፖሊስ አባላትን ጨምሮ የሰባት ሰዎች ህይወት ማለፉን የዌራ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
አደጋው ከሻሸመኔ ከተማ ወደ ቁሊቶ 10 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ በተለምዶ ዶልፊን በመባል የሚታወቅ የህዝብ ማመላለሻ መስመሩን ስቶ ከዱራሜ ወደ ሻሸመኔ በመጓዝ ላይ ካለ በተለምዶ ቅጥቅጥ ከሚባል ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የደረሰ ነው፡፡
በዚህም የሰባት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በአደጋዉ ጉዳት የደረሰባቸዉ ተጓዦች በቁሊቶ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸዉ መሆኑ ታውቋል፡፡
በዌይራ ወረዳ ፖሊስ መምሪያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር የስራ ሂደት ሀላፊ ዋና ሳጅን ባሙ ቱላ እንዳሉት በዚህ የበዓላት ሰሞን የተጓዞች ቁጥር ስለሚጨምርም ለትራፊክ አደጋ የበለጠ ተጋላጭ የመሆን ችግር እንዳይፈጠር አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ሀላፊነት መዉሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በጌታቸዉ ሙለታ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!