Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንቱን አሰናበተ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ትናንት ባካሄደው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት የነበሩትን አቶ ተሾመ ሶርሳን አሰናብቷል ።
በቅርቡ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ያካሄደውን የስራ አስፈፃሚ ምርጫ ላይ ምርጫው ህገወጥ በመሆኑ የአትዮጵያ ውሃ ስፖርት ፌዴሬሽንን በመወከል በምርጫው የሚሳተፍ ስራ አስፈፃሚ እንደማይወከል መወሰኑና መግባባት ላይ መደረሱ ተገልጿል፡፡
ሆኖም አቶ ተሾመ ሶርሳ የስራ አስፈጻሚ አባላትን ውሳኔ በመጣስና ከፌዴሬሽኑ ምንም አይነት ውክልና ሳይሰጣቸው በራሳቸው ፈቃድ ድምፅ መስጠታቸው ተረጋግጧል ተብሏል ።
ይህን ተከትሎም የኢትዮጵያ ውሃ ስፖርቶች ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ከተወያየ በኋላ ፕሬዚዳንቱ አቶ ተሾመ ሶርሳ ከስራ አስፈጻሚነታቸው ታግደው እንዲቆዩ መወሰኑን እና ውሳኔውን ጉባኤው እንዲያፀድቀው አስቸኳይ ጉባኤ መጠራቱን በጉባኤው ተገልጿል ፡፡
የፌደሬሽኑ ፕረዚዳንት የነበሩት አቶ ተሾመ ሶርሳ በቀረበው አጀንዳ ላይ የራሳቸውን ሐሳብ ያቀረቡ ሲሆን የጉባኤው ተሳታፊዎችም በቀረበው አጀንዳ ላይ ውይይት በማድረግ ውሳኔ የተላለፈ ሲሆን በዚህም ጉባኤው አቶ ተሾመ ሶርሳ ከውሃ ዋና ስፖርቶች ፕሬዚዳንትነት እንዲነሱ በአብላጫ ድምፅ መፅደቁን ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.