Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበር 57ኛውን ዓመታዊ ጉባኤ እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሀኪሞች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤውን ዛሬ ማካሄድ ጀምሯል፡፡

ለሁለት ቀን በሚቆየው ዓመታዊ ጉባኤ የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ተነስተው ለውይይት እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የኢትዮጵያ ህክምና ባለሙያዎች ማህበር የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተደረገው ርብርብ አስተዋጽዖው የጎላ እንደነበር ነው ያስረዱት፡፡

በኮቪድ-19 ምክንያት ሌሎች መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስቀጠል ረገድም የጤና ማህበሩ አስተዋጽዖ ትልቅ በመሆኑ በቀጣይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን ለማስቀጠል እና የሚሊኒየሙን የጤናው ዘርፍ የልማት ግቦችን ለማሳካት እንዲቻል የህክምና ባለሙያዎች ማህበር ያለው ድርሻ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች ወረርሽኙን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እያደረጉ ላሉት ከፍተኛ ጥረት ሚኒስትሯ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የህክምና ማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶክተር ተግባር ይግዛው በበኩላቸው የህክምና አገልግሎት ለሁሉም ተደራሽ ከማድረግ አኳያና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሀገራዊ ምላሽ አሰጣጥን በተመለከተ በቀጣይ እንደሚወያዩ ጠቅሰዋል፡፡

እንዲሁም የማህበሩን ድርሻ ለማሳደግ ለጤና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለመስጠት እንደሚሰራ  ማስታወቃቸውን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፦https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.