Fana: At a Speed of Life!

ናሳ ወደ ማርስ ሄሊኮፕተር ላከ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) ኢንጂነሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ማርስ ሄሊኮፕተር መላካቸውን አስታወቁ፡፡

በማርስ ምህዋር ዙሪያ ይበራል የተባለው ሄሊኮፕተር በመጠን እጅግ አነስተኛ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ኢንጂ ኒውቲ የተሰኘው ይህ ሄሊኮፕተር ከማርስ ወለል በሶስት ሜትር ከፍታ ላይ እንደሚበር ነው የተነገረው፡፡

ሄሊኮፕተሩ የጥቁርና ነጭ እንዲሁም ባለቀለም ምስሎችን ማንሳት የሚያስችሉ ሁለት ካሜራዎች የተገጠሙለት ሲሆን፥ የኮምፒዩተር ስርዓት፣ ባትሪና አቅጣጫ ጠቋሚም ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡

በናሳ ውስጥ ኢንጂነር የሆኑት ፋራህ አሊባይ “በምድር ላይ ለ100 ዓመታት በረናል ነገሩ ትንግርት ነው አሁን ደግሞ ወደ ሌላ ፕላኔት ሄሊኮፕተር ልንልክ ነው” ብለዋል፡፡

የሂሊኮፕተሩ ጉዞ በተለያየ ወቅት መዘግየት ቢገጥመውም ዛሬ ወደ ማርስ አቅንቷል፡፡

ወደ ማርስ የሚላከው ሄሊኮፕተር በፕላኔቷ ላይ በሚያደርገው በረራ በምድር ላይ በሚያደርገው በረራ በስምንት እጥፍ የላቀ ፍጥነት ይኖረዋል ነው የተባለው፡፡

የማርስ አየር ምድር ላይ ካለው አየር 100 ጊዜ ስስ መሆኑ ይነገራል፤ ይህም ለሄሊኮፕተሩ በረራ ችግር ከሚሆኑ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ መሆኑን ባለሙያዎቹ ጠቅሰዋል፡፡

በጥቅሉ ሄሊኮፕተሩ ከዚህ ቀደም ወደ ማርስ የተላኩ ተሽከርካሪዎች በማይደርሱባቸው በማርስ ኮረብታማ እና አነስተኛ ተራራማ ስፍራዎች ላይ አሰሳውን ያካሄዳል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.