ከ67 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ67 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የገቢና ወጪ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከመጋቢት 30 እስከ ሚያዝያ 7 ባሉት ሰባት ቀናት ውስጥ በተለያዩ የጉምሩክ ኬላዎች የተያዙ ናቸው ተብሏል፡፡
ከ36 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመተው ወደ ሀገር ሊገቡ ሲሉ የተያዙ ሲሆኑ ግምታዊ ዋጋቸው ከ30 ሚሊየን ብር የሚሆነው ከሀገር ለማስወጣት ሲሞከር የተያዙ መሆናቸው ነው የተገለጸው፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ውስጥ መድኃኒት፣ የተለያዩ ሀገራት ገንዘቦች፣ የምግብ ምርቶች፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ አልባሳት፣ መለዋወጫዎች ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን በማዘዋወር ተሳትፎ ሊኖራቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ ሶስት ግለሰቦችና ሲያጓጉዙ የተገኙ ሃያ አንድ ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!