ለሰባት ቀናት የሚቆየው የጸሎትና የምሕላ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለሰባት ቀናት የሚቆየው የጸሎትና የምሕላ መርሀ-ግብር እየተካሄደ ነው፡፡
የጋራ መርሃ ግብሩ ዛሬ በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በይፋ ታውጇል፡፡
ከነገ ጀምሮ ለተከታታይ ሰባት ቀናት የሚቆይ በሁሉም አባል የሃይማኖት ተቋማት በተናጠል የሚዘጋጅ ጸሎትና ትምህርት በሁሉም የመንግስት የሕዝብ እና የግል የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ጣቢያዎች እንደሚተላለፍም ይጠበቃል፡፡
በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን