Fana: At a Speed of Life!

አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛና ትግሪኛ ቋንቋዎች ለማሽን የማስተማር ስራ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል አማርኛ፣ አፋን ኦሮሞ፣ ሶማሊኛና ትግሪኛ ቋንቋዎች ለማሽን የማስተማር ስራ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የሰው ሰራሽ አስተውህሎ ማሽኖች ሰው ሰራሽ የማሰብ ችሎታ እንዲኖራቸው በማድረግ ካለ ሰዎች እርዳታ ራሳቸውን ችለው ስራዎችን እንዲሰሩ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀነስ ማዕከል ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በትብብር ያዘጋጁት “የሰው ሰራሽ አስተውህሎ ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል የመጀመሪያው አውደ ጥናትና አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

በቅርቡ የተቋቋመው የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በፋይናንስ፣ በትራንስፖርት፣ በጤና፣ በቋንቋ በግብርና በሌሎች ዘርፎች የሰራቸውና እየሰራቸው ያሉ ስራዎች በአውደ ጥናቱና አውደ ርዕዩ ቀርበዋል።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብረሃም በላይ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ኢትዮጵያ የያዘችውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ማዕከሉ ገና አዲስ የተቋቋመ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በብዙ ዘርፎች አበረታች ውጤቶችን እያሰመዘገበ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለቴክኖሎጂው ስርፀት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ድጋፉን አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና የኢትዮያጵን ቋንቋዎች ዓለም አቀፋዊ ለማድረግ በሰው ሰራሽ አስተውህሎ ለማሽን የማስተማር ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያን ዘመኑ በደረሰበት በሰው ሰራሽ አስተውህሎ በማህበራዊ በኢኮኖሚያዊና በፖለቲካዊ መስኮች ተጠቃሚ ለማድረግ ይሰራል ነው ማለታቸውን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል የሰው ሰራሽ አስተውህሎ ቴክኖሎጂን በኢትዮጵያ እንዲመራና እንዲደግፍ ሃላፊነት የተሰጠው ተቋም ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.