የኮቪድ 19፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የበረሃ አንበጣ ዜጎችን ለረሃብ አደጋ እንዳያጋልጡ ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የበርሃ አንበጣ እና እየተፈጠሩ ያሉ ግጭቶች ዜጎችን ለረሃብ አደጋ እንዳያጋልጥ ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ።
ይህንን ያሉት ስምንት መንግስታዊ ያልሆኑ የአውሮፓ ድርጅቶችን ያቀፈው አልያንስ 2015 በሰጠው መግለጫ ነው፡፡
አሁን ላይ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች በዓለም ላይ በተለያዩ አካባቢዎች የረሃብ አደጋ እንዲጋረጥ ምክንያት ሆነዋልም ነው ያለው።
በኢትዮጵያም ሁኔታው አስጊ ከሆነባቸው ሀገራት መካከል ተጠቃሽ መሆኗን ይፋ ባደረገው ሪፖርት አመልክቷል።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በ2030 ረሃብን ለማጥፋት የያዘው ዕቅድ የመሳካቱ ዕድልም አሳሳቢ ሆኗል ነው ያለው።
በኢትዮጵያ አሁንም የተመጣጠነ ምግብ የማያገኙ ህጻናት ቁጥር ቀላል አይደለም ሲል ገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት የነደፋቸውን የልማት ዕቅዶች በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆኑ እና የረሃብ ችግር እንዳያጋጥም መስራት ይገባልም የሚል ምክረ ሀሳብ አቅርቧል።
የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችም በኮሮና ቫይረስ እና በአየር ንብረት ለውጥ እንዳይደናቀፉ የተጠናከረ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባ የድርጅቱ የስራ ኃላፊዎች ተናግረዋል።
በስላባት ማናዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን