Fana: At a Speed of Life!

ትዊተር በጋና የአፍሪካ ጽህፈት ቤቱን ሊከፍት ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ትዊተር የአፍሪካ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን በጋና ሊከፍት መሆኑን የኩባንያው መሥራችና ሥራ አስኪያጅ ጃክ ዶርሴይ አስታወቁ፡፡

ጃክ ዶርሴይ በትዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ኩባንያው ባለሙያዎችን እየቀጠረ መሆኑንም ነው ያስታወቁት፡፡

የጋናው ፕሬዚዳንት ናና አኩፎ አዶ ውሳኔውን ተከትሎ በትዊተር መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም የሀገራቸውን የቴክኖሎጂ ዘርፍ እንደሚያነቃቃ ነው ያስታወቁት፡፡

ትዊተር ጋናን በአራት ምክንያቶች አማካኝነት መምረጡን ገልጿል፡፡

ኩባንያው ሀገሪቱን የመረጠው የዲሞክራሲ ልምምድ መዳበርና የንግግር ነጻነት በመስፈኑ መሆኑን ጠቅሷል፡፡

እንዲሁም የኦንላይን ነጻነት እና የኢንተርኔት እኩል ተደራሽነት መኖሩ ሊያስመርጣት እንደበቃ ነው ያስታወቀው፡፡

በተጨማሪም ጋና የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መቀመጫ መሆኗም ለመመረጧ እንደምክንያትነት ጠቅሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.