Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ ጠንቃቃ አሽከርካሪዎች ዕውቅና ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ ጠንቃቃ አሽከርካሪዎች ዕውቅና መሰጠቱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ጋር በጋራ በመቀናጀት በክልሉ ለሚገኙ ጠንቃቃ አሽከርካሪዎች ዕውቅና ተሰጥቷል።

እውቅናው በያዝነው በጀት ዓመት እንደርሳለን በሚል መሪ ቃል በተለያዩ የክልል ከተሞች የመንገድ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንዲሁም ለጠንቃቃ አሽከርካሪዎች የሚሰጠው እውቅና አንዱ አካል ነው።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዲኤታ ሙሉ ገብረእግዚአብሔር ሁሉም የክልል እና የፌደራል ትራንስፖርት ተቋማት፣ የብሔራዊ መንገድ ደህንነት ምክር ቤት፣ የሚዲያ አካላት፣ ታዋቂና ተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች እና የሀይማኖት አባቶች ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው በንቃት በመሳተፍ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው የትራንስፖርት ሚኒስቴር ነው፤

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.