የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሃገር አቀፍ የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብር ይፋ አደረገ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሃገር አቀፍ የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብር ይፋ ማድረጉን አስታወቀ፡፡
የጸሎትና ምህላ መርሃ ግብሩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ተሰጥቷል፡፡
የጋራ መርሃ ግብሩ ሚያዝያ 7 ከቀኑ 9 ሰዓት በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የበላይ ጠባቂ አባቶች በይፋ እንደሚታወጅ ይጠበቃል፡፡
ከሚያዚያ 8 ቀን ጀምሮም ለተከታታይ ሰባት ቀናት የሚቆይ በሁሉም አባል የሃይማኖት ተቋማት በተናጠል የሚዘጋጅ ጸሎትና ትምህርት በሁሉም የመንግስት የሕዝብ እና የግል የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ጣቢያዎች ይተላለፋል ተብሏል፡፡
በዘጠነኛው ቀንም እንደመክፈቻው ሁሉ በልዩ ዝግጅት የመዝጊያ መርሃ ግብር እንደሚካሄድ መገለጹን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን