ፕሬዚዳንት ሣህለ-ወርቅ ከተመድ የስነ-ሕዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 4፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ-ወርቅ ዘውዴ አዲሷን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስነ-ሕዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ፡፡
ተወካይዋ በሀገሪቱ ውስጥ የተጀመሩትን ማሻሻያዎች ለመደገፍ የተመድ የስነ-ሕዝብ ፈንድን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል፡፡
ሴቶችን ያካተተ እድገት ማስመዝገብ በሚቻልበት መንገድ ላይ ድርጅታቸው በተለይ ጠንክሮ እንደሚሰራ ተወካይዋ ገልጸዋል::
ፕሬዚዳንት ሣህለ-ወርቅ የተባበሩት መንግስታት የኢትዮጵያ ብሄራዊ የልማት ግቦች እንዲሳኩ በማድረግ ላይ ያለውን ጥረት ማድነቃቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፍት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን