የአማራና የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ መሪዎች በየክልሎቹ ካሉ አዋሳኝ የዞንና ወረዳ ኃላፊዎች ጋር በአዲስ አበባ መከሩ
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአማራና የኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ መሪዎች በየክልሎቹ ካሉ አዋሳኝ የዞንና ወረዳ ኃላፊዎች ጋር በአዲስ አበባ መምከራቸው ተገለጸ፡፡
የሁለቱ ክልሎች የጸጥታ ጉዳይ የውይይት መደረኩ አብይ ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡
የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብርሃም አለኸኝ ለአማራ ክልል በሱዳን በኩል የተፈጠረው ችግር፣ የትህነግ ቅሪቶች ረብሻና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የንጹሃን በጅምላ መገደል ፈተና ሆነዋል ነው ያሉት፡፡
በኦሮሚያ ክልል ወለጋ አካባቢዎች ያለውን የንጹሃን ጥቃት ለማስቆም ውይይት መደረጉንም ገልጸዋል፡፡
በኦነግ ሸኔ ላይ የፌዴራልና የክልሉ መንግሥት እየወሰዱት ያለውን ርምጃ ቀጥለው አካባቢው ሰላም ሲሆን ተፈናቃዮችን ወደ አካባቢያቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱንም ገልጸዋል፡፡
የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ፈቃዱ ተሰማ በሁለቱ ክልሎች መካከል በተቃርኖ የቆመ የመገፋፋት አካሂዶችን ወደ መልካም ተግባቦት ለመቀየር የውይይት መድረኩ ጠቃሚ መሆኑን ገልጸዋል።
በሕዝቡ ውስጥ ያሉ የጋራ እሴቶችን በመጠቀም ከተሠራው ጥላቻ ለመውጣትም ውይይቱ መካሄዱን አቶ ፈቃዱ መግለጻቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!