Fana: At a Speed of Life!

በድርጅት ስም ዕጣ ደርሷቸዋል በሚል የማጭበርበር ስራ እየተሰራ መሆኑን ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በኮካ ኮላ ድርጅት ስም ‹‹አሸንፈዋል›› በሚል የማጭበርበር ስራ እየተሰራ መሆኑን ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ “ለምርጥ ደንበኞቹ የሽልማት ፕሮግራም አዘጋጅቶ የነበረ እና ከተመረጡ ደንበኞች አንዱ እርስዎ ኖት” በሚል “የ200 ሺህ ዶላር ተሸላሚ በመሆንዎ እንኳን ደስ አለዎት” የሚል መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ይህንንም ተከትሎም ለተለያዩ ጉዳዮች ማስፈፀሚያ የሚሆን 640 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ቶሎ ይላኩ እያሉ ማጭበርበራቸውንም ገልጿል፡፡

አንዳንድ ተበዳዮች በተለያየ ጊዜና በተለያየ አካውንት 640 ሺህ የኢትዮጵያ ብር ለአጭበርባሪዎቹ ገቢ ካደረጉ በኋላ ደብዛቸውን እንዳጠፉባቸው ለኮሚሽኑ ተናግረዋል፡፡

ለአብነትም አንዲት ግለሰብ 92 ሺህ ብር በአጭበርባሪዎቹ አካውንት ላይ አስገብተው እንደተሰወሩባቸው ኮሚሽኑ ገልጸዋል፡፡

ሌላ አንድ አባት ደግሞ ከሆሮ ጉዱሩ ወለጋ 640 ሺህ ብር በተለያየ ጊዜና በተለያየ አካውንት ላይ ገቢ ካደረጉ በኋላ ተጠርጣሪዎቹ ደብዛቸው መጥፋቱን ለኮሚሽኑ አስረድተዋል፡፡

በተመሳሳይ ከአዲስ አበባ አንድ መምህር 48 ሺህ ብር በአጭበርባሪዎቹ አካውንት ካስገቡ በኋላ ጉዳዩ ማጭበርበር እንደሆነ ከደረሱበት በኋላ በድጋሚ ላኩ የተባሉትን ተጨማሪ ብር ሳይልኩ ለፖሊስ አመልክተዋል።

ይህንን የወንጀል ተግባር ለመቆጣጠርና ለማክሸፍ ፖሊስ ባደረገው ጥረት አጭበርባሪዎቹ የባንክ አካውንትና ሲም ካርድ የሚያወጡት በሀሰተኛ /Forged/ መታወቂያ እንዲሁም የሚደውሉበት የስልክ መስመርም ጁንታው ቡድን ከዚህ በፊት ለእኩይ ተግባር ባሰራጫቸው ሲም ካርዶች ጭምር መሆኑም ታውቋል።

በመሆኑም የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ዜጎች የዚህ ወንጀል ሰለባ እንዳይሆኑ እያሳሰበ መሰል የማጭበርበር ድርጊት ሲያጋጥም ብሩን ገቢ ከማድረግ አስቀድመው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመነጋገር እና ለፀጥታ አካላት በመጠቆም ህገ-ወጦችን ለህግ አስከባሪ አካላት አሳልፈው መስጠት እንደሚኖርባቸው ማሳሰቡን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.