ድሬዳዋ ለመቄዶንያ 100 ሺህ ካሬ ሜትር የመሬት ካርታ አስረከበች
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 100 ሺህ ካሬ ሜትር የመሬት ካርታ አስረከበ።
አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና በመሰብሰብ የላቀ ሰብዓዊነት ያለው መቄዶንያ ‹‹ሰው ለመርዳት ሰው ብቻ መሆን በቂ ነው›› የሚል መርህ አንግቦ ዓመታትን አስቆጥሯል።
በእነዚህ ዓመታትም በርካታ አረጋውያንንና የአዕምሮ ሕሙማንን ከጎዳና ሕይወት መታደግ የቻለ የበጎ አድራጎት ተቋም መሆኑ ይታወቃል።
ማዕከሉ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች ወገኖችን ከጎዳና በማንሳትና የተረጂዎችን ቁጥር በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ወደ 10 ሺህ ለማድረስ እየሰራም ይገኛል።
ምንጭ፡-ኢዜአ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!