Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ከጀመረ ዛሬ 75ኛ ዓመቱን ያዘ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ የጀመረበትን 75ኛ ዓመት በማክበር ላይ ይገኛል፡፡

አየር መንገዱ ከ75 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን ነበር በረራ የጀመረው፡፡

በ1938 ዓ.ም/በፈረንጆቹ 1946 የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ በረራ ከአዲስ አበባ ተነሥቶ በአስመራ በኩል ካይሮ (ግብፅ) አረፈ።

አየር መንገዱ በረራ የጀመረው ከተመሰረት ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ዛሬ በዓለማችን ከሚገኙ አንጋፋ አየር መንገዶች አንዱ ለመሆን የበቃው አየር መንገዱ 75ኛ ዓመቱን በማክበር ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

አየር መንገዱ ለደንበኞቹና ለሰራተኞቹ ለ75ኛ ዓመቱ እንኳን አደረሳቹ ብሏል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.