ቤጂንግ በቢሊየነሮች ብዛት መምራት ጀመረች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቻይናዋ ዋና ከተማ ቤጂንግ ባሏት የቢሊየነሮች ብዛት መምራት መጀመሯን ፎርብስ መፅሄት አስታወቀ፡፡
ፎርብስ በዓመታዊ ሪፖርቱ ቤጂንግ 100 ቢሊየነሮችን በመያዝ ከዓለም ከተሞች ቀዳሚዋ ሆናለች፡፡
ባለፈው ዓመት የነበራት 67 ቢሊየነሮች ሲሆን ዘንድሮ 33 ተጨማሪ ቢሊየነሮችን አፍርታለች ተብሏል፡፡
ላለፉት ሰባት ዓመታት በቢሊየነሮች ቁጥር እየመራች የነበረችው የአሜሪካዋ ኒውዮርክ ከተማ ስትሆን፥ 99 ቢሊየነሮችን በመያዝ በሁለተኛነት ትከተላለች፡፡
በሀገር ደረጃ ደግሞ አሜሪካ በዚህ ዓመትም በ724 ቢሊየነሮች እየመራች ትገኛለች፡፡
ቻይና በ698 በሁለተኛ ደረጃ ስትከተል ሕንድ 140 ቢሊየነሮችን በመያዝ ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ነው የተገለጸው፡፡
በግለሰብ ደረጃ የአማዞን መስራችና ዋና ስራ አስፈጻሚ ጄፍ ቤዞስ እስካለፈው የፈረንጆች ዓመት ድረስ 177 ቢሊየን ዶላር ሃብት በማካበት ለአራት ተከታታይ ዓመታት በቀዳሚነት ተቀምጠዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!