የጋምቤላ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላ ከተማ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው፡፡
የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ አምቢሳ ያደታ በጉባኤው መክፈቻ ላይ በከተማው ያለውን ሰላም ይበልጥ አስተማማኝ በማድረግ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ለማረጋገጥ አመራሩ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል ብለዋል፡፡
የኮሮና ወረርሽኝ ለመከላከል የምክር ቤት አባላት ህዝቡን በማስተባበር ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ጉባኤው ለሁለት ቀናት በሚኖረው ቆይታ የጋምቤላ ከተማ መስተዳድር ምክር ቤት የ6 ወራት የእቅድ ክንውን ሪፖርት መርምሮ እንደሚያፀድቅ ይጠበቃል፡፡
በተጨማሪም የከፍተኛ ፍርድ ቤትና የከተማ ምክር ቤት የ2013 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት ሪፖርቶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ይጠበቃል፡፡
በጉባኤው ላይ የጋምቤላ ከተማ መስተዳድር ምክትል ከንቲባ አቶ ዶራር ኩምን ጨምሮ የከተማ ምክር ቤት የጉባኤ አባላትና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!