Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ከ292 ሺህ በላይ ህጻናት የልጅነት ልምሻ መከላከያ ክትባት መስጠት ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፋር ክልል እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች ለሆኑ ህጻናት የልጅነት ልምሻ መከላከያ ክትባት ዛሬ መስጠት ተጀመረ።

በክልሉ ጤና ቢሮ የህጻናት ክትባት ንኡስ ስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አወል ጉደሌ ፤  ክትባቱ በሁሉም የክልሉ ወረዳዎች ውስጥ ይሰጣል ብለዋል ።

እድሜያቸው ከአምስት በአመት በታች ለሆኑ ከ292 ሺህ 437 ህጻናት ክትባቱ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ቀንናት እንደሚሰጥ ተናግረዋል ።

ክትባቱ ከሚሰጣቸው ህጻናት ውስጥ 6 ሺህ 421ዱ በአይሳኢታና በራህሌ የኤርትራ ስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች  የሚገኙ መሆናቸውን አመልክተዋል ።

ክትባቱን ከእድሜ ክልሉ በታች ለሆኑ ሁሉም ህጻናት ተደራሽ ለማድረግ ከመድሀኒት አቅርባትና ባለሙያ ጀምሮ በቂ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀዋል ።

ህብረተሰቡ ልጆቹን በማስከተብ ከአካል ጉዳተኝነት እንዲታደግ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በክልሉና አጎራባች በሆነው በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን  ከዚህ ቀደም በቫይረሱ የተጠቁ ህጻናት መገኘታቸውን ተከትሎ በህዳር 2013 ዓም ከአማራ ክልል አጎራባች በሆኑ  አውሲ-ረሱ፣ ገቢ-ረሱና ሀሪ-ረሱ የአፋር ዞኖች ክትባቱ በዘመቻ መሰጠቱን አስታውሰዋል ።

እንደ አስተባባሪው ገለጻ በክልሉ ዛሬ የተጀመረው ክትባት በመደበኛ መርሀ ግብር የሚሰጥ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.