ጣልያን በኮቪድ 19 ምክንያት ዳግም ጥብቅ ክልከላዎችን አስተላለፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣልያን በኮቪድ 19 የሚያዙ ዜጎቿ ቁጥር ማሻቀቡን ተከትሎ ዳግም ጥብቅ ክልከላዎችን አስተላለፈች፡፡
በሀገሪቱ በአማካይ ከ20 ሺህ ሰዎች በላይ በወረርሽኙ እየተያዙ ይገኛሉ ተብሏል፡፡
የሦስተኛው ዙር የወረርሸኙ ስርጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱም ተነግሯል፡፡
የፋሲካ በዓልን ለማክበር ወደተለያዩ ግዛቶች እንዳይጓዙም ገደብ ተጥሏል፡፡
የሮማ ካቶሊካዊት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳ ፍራንሲስ ቡራኬያቸውን ምዕመናን በሌሉበት በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ እንደሚያስተላልፉም ይጠበቃል፡፡
የተጣለውን ገደብ የሚከታተሉ ተጨማሪ 70 ሺህ ፖሊሶች በመላው ሀገሪቱ እንደተሰማሩም ተገልጿል፡፡
በጣልያን እስካሁን 110 ሺህ 328 ሰዎች በወረርሽኙ አማካኝነት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በአውሮፓ የወረርሽኙ መዛመትና የኮሮና ቫይረስ ክትባት መዘግየት አሳሳቢ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
ከጣልያን በተጨማሪ ፈረንሳይም በመላው ሀገሪቱ የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሏንም ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!