Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞችና ሃላፊዎች በእሳት የተፈተኑ የልማት አርበኞች ናቸው – ዶ/ር አረጋዊ በርሔ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ሰራተኞችና ሃላፊዎች በእሳት የተፈተኑ የልማት አርበኞች ናቸው ሲሉ የግድቡ ህዝባዊ ተሳትፎ አስተባባሪ ብሔራዊ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሔ ገለጹ።

ኢትዮጵያ ለውጥ ውስጥ ከገባች ወዲህ መንግስት ግድቡን ለማጠናቀቅ በሙሉ አቅሙ እየሰራ እንደሆነም ተናግረዋል።

መንግስት በቁርጠኝነት በመስራት የግድቡ ግንባታ ሂደት ከነበረበት ውስብስብ ችግር ውስጥ ወጥቶ አሁን የሚያኮራ ደረጃ ላይ እንዳደረሰውም ገልጸዋል።

“በግድቡ ግንባታ ሂደት እየተሳተፉ የሚገኙ ሰራተኞችና የስራ ኃላፊዎች በእሳት የተፈተኑ የልማት አርበኞች ናቸው ማለት ይቻላል” ያሉት ዶክተር አረጋዊ፤ ሰራተኞችና ሃላፊዎች የአካባቢውን ከፍተኛ ሙቀት ተቋቁመው ያለ እረፍት እየሰሩ እንደሚገኙም ነው ያስረዱት።

ግድቡን በሚቀጥሉት ሁለትና ሶስት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሰራ እንደሆነ ጠቁመው፤ ሁሉም ኢትዮጵያውያን እጅ ለእጅ በመያያዝ የጋራ አሻራቸው ያረፈበት ግድብ እስኪጠናቀቅ የሚያደረጉትን የገንዘብ፣ የእውቀትና የጉልበት ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.