Fana: At a Speed of Life!

በብራዚል በመጋቢት ወር ብቻ ከ60 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ 19 ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23፣ 2013 (ኤፍ ቢሲ) በብራዚል በመጋቢት ወር ብቻ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 66 ሺህ 570 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ተገለጸ፡፡

ይህም ካለፈው ወር ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ ጨምሯል ነው የተባለው፡፡

የብራዚሉ ፕሬዚዳንት ጃዬር ቦልሶናሮ ወረርሽኙን ለመከላከል ባሳዩት ቸልተኝነት ምክንያት ስልጣናቸውን እንዲለቁ ግፊት እየበረታባቸው ይገኛል፡፡

የሃገሪቱ ከፍተኛ ባለስልጣናትም ስልጣናቸውን በገዛ ፍቃዳቸው መልቀቃቸው ተሰምቷል፡፡

ሆኖም ፕሬዚዳንቱ በሃገረ ገዢዎች ዳግም የተጣሉትን አዳዲስ ክልከላዎች አጣጥለዋል፡፡

ወረርሽኙና ስራ አጥነት የሀገሪቷ አንገብጋቢ ጎዳዮች እንደሆኑ ያነሱት ፕሬዚዳንቱ ይህንን ደግሞ በራችን ዘግተን በመቀመጥ አንፈታውም ብለዋል፡፡

በሃገሪቱ በትናንትናው ዕለት ብቻ 90 ሺህ ሰዎች በወረርሽኙ ሲያዙ 3 ሺህ 800 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ አማካኝነት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.