የዋልያዎቹን የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ የሚወስነው ጨዋታ 10 ሰአት ላይ ይደረጋል
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከኮቲዲቯር አቻው ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
ጨዋታው ኢትዮጵያ ከስምንት አመታት በኋላ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋን የምትወስንበት ወሳኝ ጨዋታ ነው፡፡
ከሰአት በኋላ በሚደረገው ጨዋታ ዋልያዎቹ ከጨዋታው ነጥብ ይዘው መውጣት ከቻሉ ቀጣዩን የአፍሪካ ዋንጫ ይቀላቀላሉ፡፡
በጨዋታው ማሸነፍ፣ አቻ መውጣት አልያም ከኒጀር ጋር የምትጫወተው ማዳጋስካር ነጥብ ከጣለች የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎውን ያረጋግጣል፡፡
በምድቡ ኮቲዲቯር 10 ነጥብ በመያዝ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን ስታረጋግጥ ኢትዮጵያ 9 ነጥቦችን በመያዝ ትከተላለች፡፡
ማዳጋስካር 7 እንዲሁም ኒጀር 3 ነጥብ ይዘዋል፡፡
ኢትዮጵያ እና ኮቲዲቯር ባደረጉት የመጀመሪያ ዙር ጨዋታ ዋልያዎቹ 2 ለ 1 ማሸነፋቸው የሚታወስ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!