በኳታር በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ላይ የሚያተኩር ውይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኳታር በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዙሪያ የሚያተኩር የቪዲዮ ኮንፈረንስ ውይይት ተካሄደ፡፡
የቪዲዮ ኮንፈረንሱን በዶኻ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኮን ከተባለ የቢዝነስ ስራዎች አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ያዘጋጁት፡፡
በውይይቱ በዋናነትም የኢትዮጵያና የኳታር የንግድ ግንኙነት እንደተዳሰስም ተገልጿል፡፡
ከዚህ ባለፈም በኢትዮጵያ ዋነኛ የንግድ አማራጮች እና ለውጭ ባለሃብቶች የተመቻቸው ዕድል ላይ ውይይት ተደርጓል፡፡
በውይይቱ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የኳታር ባለሃብቶች፣ የኤምባሲው ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳታፊዎች ናቸው፡፡
ኢትዮጵያ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ከ10 የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንደኛዋ መሆኗን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!