Fana: At a Speed of Life!

የኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለአፍሪካ ብሎም ለኢትዮጵያ በኦሎምፒክ መድረክ በ10 ሺህ ሜትር በባርሴሎና የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳልያ ባለቤት ለሆነች ለኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ የዕውቅናና ምስጋና መርሀ ግብር ተካሄደ።

በስነ ስርዓቱ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል፣ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ፣ አዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ታዋቂ አትሌቶች ፣ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በፈረንጆቹ 1992 የባርሴሎና ኦሊምፒክ ኢትዮጵያን በ10 ሺህ ሜትር ውድድር በመወከል በሴቶች ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።

ከዚህ ውጤት በኋላ በኦሊምፒኮች፣ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች፣ በአለም አገር አቋራጭ ውድድሮች፣ በኮንቲኔንታል ካፕ፣ ከ20 አመት በታች የአለም ሻምፒዮና፣ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች፣ በአለም አትሌቲክስ ፋይናል፣ በጎልደን ሊግ፣ በኢንተርናሽናል ማራቶን እና በኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ሻምፒዮናዎች ከ13 በላይ ወርቆች፣ 2 ብሮች፣ 1 ነሃስና 3 ዲፕሎማዎችን ለሃገሯ አበርክታለች።

ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ተሰማርታ በተለያዩ አካባቢዎች ሆቴልና መዝናኛዎችን ገንብታ ለበርካታ ኢትዮጵያውያን የሥራ እድል መፍጠር ችላለች።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.