ደሴቷ ሀገር ኮሞሮስ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደሴቷ ሀገር እና 900 ሺህ ህዝብ ብቻ ያላት ኮሞሮስ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች።
ከቶጎ ብሄራዊ ቡድን ጋር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት መለያየቷን ተከትሎ ደሴቷ ሀገር በካሜሩን አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ አልፋለች።
5 ጨዋታዎችን አድርጋ 9 ነጥብ በመሰብስ በምድቧ በግብ ክፍያ ተበልጣ ከግብፅ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
በመሆኑም በምድቡ 3 እና 4ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ኬንያ እና ቶጎ 4 ና 2 ነጥቦችን ብቻ በመሰብሰባቸው ኮሞሮስ ምርጥ ሁለተኛ ሆና ወደ አፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋግጣለች።
ኮሞሮስ ቀጣዩን የምድብ ጨዋታ ከምድቡ መሪ ግብፅ ጋር በካይሮ ታደርጋለች።
በተመሳሳይ ጋምቢያም ለመጀመሪያ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎን አግኝታለች፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን