Fana: At a Speed of Life!

በምሥራቅ ወለጋ ዞን ከ114 ሚሊየን በላይ የቡና ችግኝ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ክረምት የሚተከል ከ114 ሚሊየን በላይ የቡና ችግኝ መዘጋጀቱን የምሥራቅ ወለጋ ዞን የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡

ምስራቅ ወለጋ  ለቡና ልማት ተስማሚ የአየር ንብረትና አመቺ ስነ ምህዳር ያለው ዞን እንደሆነ ተመልክቷል።

አርሶ አደሩም በግብርና ባለሙያዎች በመታገዝ ያረጀውን ቡና በማስወገድ  ምርታማነት የሚጨምሩና በሽታን የሚቋቋሙ የቡና ችግኞችን ሲተክል መቆየቱን በጽህፈት ቤቱ የቡና የቅመማ ቅመምና ፍራፍሬ ልማት ቡድን መሪ አቶ አሰፋ መኮንን ተናግረዋል።

በመጪው ክረምትም በሽታን ተቋቁሞ ምርት የሚሰጥ ከ114 ሚሊዮን በላይ ችግኝ  መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

ችግኙ የተዘጋጀው በ11ሺህ የመንግሥት፣መንግስታዊ ያልሆኑ ደርጅቶችና የግል ችግኝ ጣቢያዎች እንደሆነ ያመለከቱት አቶ አሰፋ፤ በአዲስ መሬት እና ነባር ይዞታዎች ላይ የሚተከል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

በማሳቸው ቡናን ከማልማት ባሻገር ችግኙን ለገበያ እያቀረቡ ገቢያቸውን እያሳደጉ ያሉ አርሶ አደሮችም አሉ ብለዋል።

ከአርሶ አደሮቹ መካከል በሳሲጋ ወረዳ የጌላ ቀርሳ ቀበሌ ነዋሪ  ጌታቸው ኢዶሳ በሰጡት አስተያየት ለመጪው ክረምት በግላቸው 150 ሺህ የቡና ችግኝን በማዘጋጀት እየተንከባከቡ  መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ያዘጋጁትን የቡና ችግኝ ለገበያ አቅርበው በመሸጥ   የተሻለ ገቢ ለማግኘት ማቀዳቸውንም ገልጸዋል፡፡

በወረዳው  የሀሮ ጉዲና ቀበሌ አርሶ አደር ጥሩነህ ኡልፊና በበኩላቸው ባለፈው ዓመት   ከቡና ችግኝ ሽያጭ 15 ሺህ ብር ገቢ ማግኘታቸውን አስታውሰዋል።

በዚህ ዓመትም 20ሺህ የቡና ችግኞችን በማዘጋጀት ከሽያጩ ተጨማሪ ገቢ  እንደሚጠብቁ ኤዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.