ምክር ቤቱ እየተሻሻለ የቆየውን የንግድ ህግ ረቂቅ አዋጅ አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ34 ዓመታት እየተሻሻለ የነበረው የንግድ ህግ ረቂቅ አዋጅ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤተር ጸደቀ፡፡
ረቂቅ አዋጁ ላለፉት 62 ዓመታት በስራ ላይ የነበረውና ከ1979 ዓ.ም ጀምሮ ማሻሻያ ሲደረግበት ቆይቶ በተለያየ ምክንያት ሳይቋጭ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ባለፈው አንድ ዓመት ተኩል በዝርዝር ማሻሻያ ሲደረግበት ቆይቶ ዛሬ በሕዝብ ተወካዮች ክር ቤት በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡
በረቂቅ ሕጉ 825 አንቀጾች ማሻሻያ የተደረገላቸው ሲሆን ከነበረው የንግድ ሕግ አዋጅ ላይ ማሻሻያው ያካተተው የንግዱን ዘርፍ ብቻ ነው፡፡
አዲስ የጸደቀው የንግድ ህግ አዋጅ ወቅቱን ያገነዘበና ቴክኖሎጂውንም ታሳቢ አድርጎ ለቀጣይ 30 ዓመታት እንደሚያገለግል ይጠበቃል፡፡
በአዋጁ በአንድ ግለሰብ የሚመራ የህብረት ስራ ማህበርን የሚፈቅድ ሲሆን በአነስተኛ መጠን የሚሰሩ ሰዎችና የእርሻና የደን ልማት ላይ የተሰማሩ ሰዎችን በሚቀመጥ መስፈርት በንግድ ስርዓት ውስጥ እንዲመዘገቡ አያስገድድም፡፡
በንግድ ስርዓት ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ግለሰብም ሆነ ድርጅት በህግ የተከለከለ ካልሆነ በስተቀር በንግድ ስርዓቱ እንዲሳተፉ ይፈቅዳል፡፡
በንግድ ስርዓት ውስጥ ለመሳተፍ የሚፈልግ አካል አጭርና ቀልጣፋ የንግድ ፍቃድ አወጣጥ አገልግሎት እንዲያገኝ አዋጁ እንደሚያስገድድ ተገልጿል፡፡
በሃይለኢየሱስ ስዩም
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን