Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ የተመድን ውሳኔ ችላ በማለት የሚሳኤል ሙከራ አደረገች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ ሁለት የሚሳኤል ሙከራዎችን አደረገች፡፡

ሚሳኤሉ ወደ ጃፓን ባህር ክልል የተደረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የአሁኑ ሙከራ ከዚህ ቀደም የተባበሩት መንግስታት የጸጥታው ምክር ቤት ያሳለፈውን ውሳኔ ወደ ጎን በማለት የተካሄደ ነው ተብሏል፡፡

ሙከራውን ተከትሎ ደቡብ ኮሪያና ጃፓን ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

በእስያ ፓሲፊክ አካባቢ ያለው የአሜሪካ ፓሲፊሲክ ዕዝ ሙከራው ለቀጠናውና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ስጋት ነው ብሎታል፡፡

ጃፓን እንዳስታወቀችው ከሆነ ሚሳኤሎቹ 420 እና 430 ኪሎ ሜትር ርቀት ይወነጨፋሉ፡፡

ሰሜን ኮሪያ ለመጨረሻ ጊዜ የሚሳኤል ሙከራ ያደረገችው ባለፈው ዓመት እንደነበር ይታወሳል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.