የኬንያ አየር መንገድ የ333 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ደረሰበት
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ አየር መንገድ ባለፈው የፈረንጆቹ አመት የ333 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ እንደደረሰበት አስታወቀ፡፡
የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አላን ኪላቩካ በፈረንጆቹ 2019 በአየር መንገዱ የተጓዦች ቁጥር 5 ነጥብ 2 ሚሊየን እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
ይህ አሃዝ በ2020 ወደ 1 ነጥብ 9 ሚሊየን እንደወረደ ነው ያስታወቁት፡፡
በተጨማሪም 70 በመቶዎቹ ተጓዦችም ቢሆኑ በ2020 የመጀመሪያዎቹ ሦስት ወራት የተጓጓዙ ናቸው ብለዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው የኮሮና ቫይረስ ተጽዕኖ ከባድ እንደነበር ጠቅሰው አየር መንገዱ አሁን ከደረሰበት ኪሳራ ለመውጣት ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
በኪሳራው ምክንያት አየር መንገዱ አጠቃላይ አሴቱ ወደ 12 በመቶ ማሽቆልቆሉም ተነግሯል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን