Fana: At a Speed of Life!

ኦነግ ያስገባውን ሰነድ ተከትሎ ቦርዱ መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር /ኦነግ/ ያስገባውን ሰነድ ተከትሎ መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ አስታወቀ፡፡

ኦነግ በአቶ አራርሶ ቢቂላ በተጻፈ ደብዳቤ ሁለተኛውን ጠቅላላ ጉባዔ መጋቢት 4 ቀን 2013 ዓ.ም ማካሄዱን በሰነዱ ገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎም መተዳደሪያ ደንቡን ማሻሻሉን፣ የፓርቲውንም ብሔራዊ ምክር ቤት መምረጡን ሰነዱ ያስረዳል፡፡

እንዲሁም በማግስቱ መጋቢት 5 ቀን 2013 ዓ.ም. የድርጅቱን ብሔራዊ ምክር ቤት ተሰብስቦ የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች መምረጡን ያስረዳሉ የተባሉ ሠነዶች ዛሬ ለቦርዱ አስገብቷል፡፡

ቦርዱም ይህንን ተከትሎ ኦነግ ያስገባቸውን ሰነዶች እንደሚመረምር እና አስፈላጊውን ውሳኔ እንደሚሰጥ ገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.