የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን የፕሪሚየር ሊጉ ሻምፒዮን ሆነ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሴቶች እግር ኳስ ቡድን አንድ ጨዋታ እየቀረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋገጠ፡፡
በ17ኛው ሳምንት የሊጉ ውድድር አዳማ ከተማን 2 ለ 1 መርታቱን ተከትሎ ነው ሻምፒዮናነቱን ያረጋገጠው፡፡
በውድድር ዘመኑ ቡድኑ 43 ነጥቦችን መሰብሰቡን ከንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተጨማሪም የቡድኑ ተጫዋቾች ረሂማ ዘርጋው በ16 እና ሎዛ አበራ በ15 ግቦች የኮከብ ግብ አግቢነቱን ደረጃ አንደኛና ሁለተኛ በመሆን እየመሩ ይገኛሉ፡፡
ፕሪሚየር ሊጉ መጋቢት 19 ቀን በአዳማ ከተማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን